እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች

በአሁኑ ወቅት ድርጅታችን በተለያዩ የከተማችን ክፍሎች የተጀመሩ ግንባታዎችን በከፍተኛ ትኩረት በመከታተል ላይ ይገኛል። እነዚህ ፕሮጀክቶች እንደየደረጃቸው በጥራት ቁጥጥር እየተደረገባቸው ሲሆን፣ የተወሰኑትም በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ በመገኘት በቅርቡ ለተጠቃሚዎች ምቹ እንዲሆኑ ተደርገው ያልቃሉ። ለምሳሌ ያህል፣ በ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው የ ዋና ላይብሬሪ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን፣ በቅርቡም የምረቃ ስነ-ስርዓት ይከናወናል።

Gallery

መንግስቱ መንገሻ ህንፃ ስራ ተቋራጭ በዋናነት በግንባታ ስራ ላይ የተሰማራ ቢሆንም፣ በተለያዩ ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍና የተቸገሩትን በመርዳት በጎ ተግባራትን በመፈፀም ይታወቃል።

Gallery

ድርጅታችን ባከናወናቸው የልማት ሥራዎች ጥራትና ታማኝነት በተለያዩ ጊዜያት ከበርካታ ድርጅቶችና ከመንግስት መስሪያ ቤቶች የእውቅና ሰርተፊኬቶችንና የዋንጫ ሽልማቶችን ተቀብሏል። በተለይም በክልሉ ካሉ ታማኝ ግብር ከፋዮች መካከል በግንባር ቀደምትነት በመመዝገብ የዋንጫ ሽልማቶችን በተደጋጋሚ አሸንፏል። ይህንንም ስኬት ወደፊት በማስጠበቅና በማሻሻል ለክልሉ የተሻለ ገቢ ለማስገባት የድርጅቱ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል።

Gallery

ድርጅታችን ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ግንባታን በሰዓቱ ለማጠናቀቅ የሚያስችል የራሱ የሆኑ በርካታ ማሽኖችና ተሽከርካሪዎች ባለቤት ነው። ይህንን አቅማችንን በመጠቀም ጥራቱን የጠበቀ ስራን በተመደበው ጊዜ ውስጥ በማድረስ ለደንበኞቻችን እርካታን እናረጋግጣለን። ዘመናዊ ቁሳቁሶችን በመጠቀም የተሻለ ጥንካሬ እና ዘላቂነት ያላቸውን ግንባታዎች በመስራት የገበያ ተወዳዳሪነታችንን አጠናክረናል።

Gallery