መንግስቱ መንገሻ ሕንፃ ስራ ተቋራጭ
Mengistu Mengesha Construction
መንግሥቱ መንገሻ ሕንፃ ሥራ ተቋራጭ፣ የደንበኞቻችንን እርካታ ቀዳሚ ትኩረታችን አድርገን፣ በጀትና ጊዜን ጠብቀን ጥራት ያለው ሥራ እንሰራለን
10+ Years Of Undefeated Success
መንግሥቱ መንገሻ ሕንፃ ሥራ ተቋራጭ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ከ10 ዓመታት በላይ በግንባታ ዘርፍ ያለምንም ማቋረጥ ሲሰራ ቆይቷል። ድርጅቱ በትንንሽ ፕሮጀክቶች ተጀምሮ ዛሬ ላይ እጅግ ግዙፍ የሆኑ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እስከመገንባት ደርሷል። ይህ የዕድገት ጉዞ የድርጅቱን ቁርጠኝነት፣ ሙያዊ ብቃትና ለደንበኞች ያለውን ታማኝነት የሚያሳይ ነው።
በእነዚህ ዓመታት ውስጥ መንግሥቱ መንገሻ ሕንፃ ሥራ ተቋራጭ በርካታ የመኖሪያና የንግድ ህንፃዎችን በመገንባት፣ እንዲሁም የተለያዩ የማማከር አገልግሎቶችን በመስጠት ለማህበረሰቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል። ድርጅቱ ጥራትን፣ ፍጥነትንና የደንበኞችን እርካታን በማስቀደም ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀምና የሰለጠነ የሰው ኃይልን በማሰማራት ተወዳዳሪነቱን አረጋግጧል። በቀጣይም ለህብረተሰቡ ዘላቂና ተደራሽ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ቁርጠኛ ነው።
30+
Successful Projects.
10+
Years of experience with proud
Services
01 Service
ትላልቅ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን መገንባት
መንግሥቱ መንገሻ ሕንፃ ሥራ ተቋራጭ ለክልልና ለፌዴራል መንግስታት ዘመናዊና ደረጃቸውን የጠበቁ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን በመገንባት ሰፊ ልምድ አለው። ድርጅቱ የመንግስት መስፈርቶችን በማሟላት፣ በጀትና ጊዜን ጠብቆ ጥራት ያለው ሥራ ያቀርባል።
02 Service
የንግድ ኮምፕሌክስ ህንፃዎች መገንባት
ድርጅቱ ለግል ባለሀብቶች ዘመናዊ የንግድ ኮምፕሌክስ ህንፃዎችን በመገንባት ይታወቃል። ደንበኞቻችን የንግድ ፍላጎታቸውን የሚያሟሉ፣ ምቹና ዘመናዊ የሆኑ ህንፃዎችን እንዲያገኙ እናግዛለን። ከዲዛይን እስከ ግንባታ ድረስ ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ቦታ እናቀርባለን።
03 Service
ጅምላ ሲሚንቶ እናቀርባለን
ጥራት ያለው የለሚ ናሽናል ሲሚንቶን በመላው ኢትዮጵያ ላሉ አከፋፋዮች በጅምላ በማቅረብ ላይ እንገኛለን። ለግንባታ ፕሮጀክቶችዎ አስተማማኝ አጋር በመሆን ተወዳዳሪ ዋጋ እና የተረጋጋ አቅርቦትን እናረጋግጣለን። ከፍተኛ ጥራት ያለው የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ በተመጣጣኝ ዋጋ ወቅቱን በጠበቀ እና በአስተማማኝ አቅርቦት መላው ሀገሪቱ የማድረስ አገልግሎት እንሰጣለን።
04 Service
ጠጠር ማምረቻ
መንግስቱ መንገሻ ህንፃ ስራ ተቋራጭ ጥራት ያለው የጠጠር ምርት በስፋት በማምረት ለራሱ የግንባታ ፕሮጀክቶች ከመጠቀም ባለፈ ለሌሎችም የግንባታ ድርጅቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባል። ይህ አገልግሎት እንደ ደንበኞቻችን ፍላጎት የተለያዩ መጠን ያላቸውን ጠጠሮች በወቅቱ በማቅረብና በተወዳዳሪ ዋጋ በመሸጥ የግንባታ ስራዎቻቸውን በተሳካ ሁኔታ እንዲያጠናቅቁ ያግዛል። ለበለጠ መረጃ ወይም ትዕዛዝ ለማስተላለፍ እባክዎን ያነጋግሩን።
05 Service
የወርቅ ቁፋሮ ስራ
በወርቅ ቁፋሮ ዘርፍ የመንግሥቱ መንገሻ ሕንፃ ሥራ ተቋራጭ አስፈላጊ የሆኑ ማሽኖችና መሳሪያዎችን በመጠቀም ስራችንን በመስራት ላይ እንገኛለን። ይህ ስራችን ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠሩም በላይ በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንዱስትሪ ውስጥ አዲስ ተሳትፎን እያሳየን ነው። ከህንፃ ስራ ዘርፍ ባለፈ በወርቅ ቁፋሮው ዘርፍም መሳተፋችን የንግድ ስራችንን ወሰን እያሰፋ መምጣቱን ያሳያል።
06 Service
የማማከር አገልግሎት
የተለያዩ የህንፃ ግንባታ አይነቶችን በተመለከተ ማማከርን ይሰጣል። የመኖሪያ ህንፃዎች፣ የንግድ ህንፃዎች፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ሌሎች ልዩ ልዩ ህንፃዎች የህንፃ ግንባታ ላይ የሚያጋጥሙ የተለያዩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ምክሮችን ይለግሳል።
ጤናማና ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመገንባት እንተጋለን!
በግንባታዎቻችን ወቅት የአካባቢን ደህንነት በመጠበቅና ዘላቂነትን በማረጋገጥ ለትውልድ የሚተላለፍ ሀብት እንገነባለን።
ምርጥ የአሰራር ዘዴዎችን እንከተላለን
በእያንዳንዱ ፕሮጀክት ላይ ምርጥ የአሰራር ዘዴዎችን በመከተል የደንበኞቻችንን እርካታ እናረጋግጣለን።
- ዘላቂነት
- ፕሮጀክት በጊዜው ማጠናቀቅ
- ዘመናዊ ቴክኖሎጂ
- ዘመናዊ ንድፍ
Our Latest Works
Administration Office
Gimbo Woreda
Bonga University
Gesha Research Center
Cultural Hall
Gesha Woreda
Bonga University Main Library
Kaffa, Bonga




















